ጠ/ሚ ዐቢይ ከፌደራል እና ከክልል አመራሮች ጋር በመጪው ምርጫ ዙሪያ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፌደራል እና ከክልል አመራሮች ጋር በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ዙሪያ መወያየታቸውን አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች እና ኃላፊነቶች አንድ ተደርገው እንዳይቆጠሩ ግልጽ መለያዎች መቀመጣቸውን ነው የገለጹት፡፡በዚህ ምርጫ የመንግሥት ኃላፊነት ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነው ብለዋል። በዚሁ መሠረት፣ የክልል ብሔራዊ መንግሥታትም በምርጫው ሂደት ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማገዝ ቁርጠኝነት ማሳየታቸውንም በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡