ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የስራ ጉብኝት ጅማ ገብተዋል

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት የስራ ለማድረግ ጅማ ከተማ ገብተዋል።ፕሬዚዳንቱ ጅማ አባ ጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋርም ከኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ እና የአማካሪያቸው የማነ ገብረዓብ ኢትዮጵያ ገብተዋል።ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና የቀጠናው ሀገራት ትስስር ላይ እንደሚወያዩ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።