ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለስራ ጉብኝት ቡሩንዲ ገቡ

ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቷ ቡጁምቡራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኤቭሪስቴ እንዴይሺምዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዘዳንት ሣህለ ወርቅ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያና ቡሩንዲ የቆየ ወዳጅነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ መስኮች የሚያደርጉትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራም ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በቡጁምቡራ ከተማ በሚገኘው የቡሩንዲ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጀግኖች ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን ማኖራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።