InternationalNews

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን የኢራንን ጦርነት ማስቆም በሚያስችለው የመግባቢያ ስምምነት ላይ መፈራረማቸው ተነገረ።

በዚህ ባለ 14 ነጥቦች የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ 60 ቀናት ውስጥ በተጨማሪ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር አሳሪ ስምምነት ላይ እንደሚደርሱም ነው የሚጠበቀው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዚህ የመግባቢያ ስምምነት ላይ የፈረሙት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ባሰናዱት የእራት ግብዣ ላይ ሲሆን ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያንም ካሉበት ቴህራን በስምምነቱ ላይ የኤሌክትሮኒክ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ በይፋ የሚፈራረሙት በነገው ዕለት በስዊዘርላንድ ሲሆን በአሜሪካ በኩል የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እንዲሁም በኢራን በኩል የሀገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሞሀመድ ባጌር ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv