Sports

ሀዋሳ ከተማ ኤፍሬም አሻሞን አስፈረመ

መስመር አጥቂው ኤፍሬም አሻሞ ከመቐለ 70 እንደርታ ወደ ሀዋሳ ከተማ በአንድ አመት ውል ተዘዋውሯል፡፡

በቀድሞ ተጫዋቹ ሙሉጌታ ምህረት የሚሰለጥነው ሃዋሳ ከኤፍሬም አሻሞ በተጨማሪም ከደቡብ ፖሊስ ተከላካዩ ዘነበ ከድር እና ግብ ጠባቂውን ዳግም ተፈራ (ቻቺ) በአዲስ ውል ፈርመው ውላቸው ፀድቋል፡፡

በተመመሳሳይ ክለቡ ሰሞኑን የበርካታ ተጨዋቾችን ውል ያራዘመ እና አዲስ ተጨዋቾች ማስፈረሙን ከኢትዮ ኪክ ኦፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።