ሃሰተኛ መድኃኒቶች
በአፍሪካ በታማሚዎች ከሚወሰዱ መድኃኒቶች አንድ አምስተኛው ወይም 20 በመቶው ትክክለኛ ያልሆኑ ወይም ከደረጃ በታች መሆናቸውን አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡
በባህርዳር ዩንቨርሲቲ የተጠናውን ጥናት ዋቢ አድርጎ ዘጋርዲያን እንደዘገበው ናሙና ከተወሰዱ 7 ሺ 508 መድሃኒቶች 1 ሺ 639 የሚሆኑት ዝቅተኛ የጥራት ደረጃን የማያሟሉ ወይም ሃሰተኛ ሆነው መገኘታቸው ተረጋግጧል፡፡
ጥናቱን ያሰራው መቀመጫውን አምስተዳርዳም ሆላንድ ያደረገው አክሰስ ቱ ሜዲሲን የተሰኘው አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ሲሆን የጥናቱን ውጤትም አሳሳቢ የህበረተሰብ ጤና ጉዳይ ነው ብሎታል፡፡