InternationalNews

ማሳሰቢያ ለአሜሪካ ዜጎች

በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በኢራቅ የሚገኙ አሜሪካዊያን በአፋጣኝ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

ኤምባሲው በቀጣይ 48 ሰዓታት ውስጥ በባግዳድ ከተማ ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው የኢራቅ ሚሊሻዎች በአሜሪካዊያንና በአሜሪካ ጥቅሞች ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ መዘጋጀታቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

አሜሪካዊያን፣ ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ዲፕሎማሲያዊ ጽህፈት ቤቶች፣ የኢነርጂ መሰረተ ልማት፣ ሆቴሎችና አየር ማረፊያዎች እንዲሁም የኢራቅ ተቋማት የታጣቂዎቹ ኢላማ ናቸው ማለቱን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews