LatestNews

በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ የሽብር አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ::

በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 15 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ :: ከውጭ የሽብር ቡድን አባላት ተልዕኮ በመቀበል አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት በመፈጸም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ 15 የሽብር ቡድን አባላት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ገለጿል።ተጠርጣሪዎቹ የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የዲፖሎማሲ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን የአዲስ አበባን በጎ ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ እንዳሉ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ባደረገው የተቀናጀ ክትትል ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች ፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ግለሰቦቹ ለጥቃት ሊጠቀሙባቸው ያዘጋጇቸው ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችና ለፍንዳታ ተግባር የሚውሉ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶች በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት መገኘታቸውንም ተቋሙ አስታውቋል።ሌላ ተመሳሳይ ተልዕኮ የተሠጠው ህቡዕ ቡድንም በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኤምባሲ ላይ ተመሳሳይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የጠቆመው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የግንኙነት መረቡን ለመበጣጠስ እንዲሁም ተጠርጣሪዎችን አስሶ ለመያዝ ከሱዳን የመረጃና የደህንነት ተቋም ጋር በቅንጅት መሰራቱን ጠቁሟል።