EthiopiaNews

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት ለምትፈልጉ

በመደበኛ መርሓ ግብር በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በፒ.ኤች.ዲ ደረጃ መሰልጠን የምትፈልጉ ማመልከት ትችላላቹ ተብሏል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት ለ2017 ዓ.ም በመስኩ ሰልጣኞችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት ስለማድረጋቸው አስታውቀዋል፡፡

የኘሮግራሙ ዓላማ በዘርፉ ያለውን የተመራማሪዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች እጥረት መቅረፍ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ለኘሮግራሙ ስኬት ሁለቱ ተቋማት በከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ለዝርዝር መረጃ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ድረ ገጽና ማህበራዊ ገጽ https://t.me/EthiopianAII ይመልከቱ