ባእድ ነገር የተቀላቀለበት ዘይት በአዲስ አበባ ተያዘ።
ባእድ ነገር የተቀላቀለበት 200 ያህል ባለ 20 ሊትር ዘይት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ነው ያስታወቀው ።
ዘይት በመግዛት ወደ ክልል ከተማ አስጭኖ የተጓዘ ነጋዴ ዘይቱን ለገበያ ሲያቀርብ ትክክለኝነቱንና ንፅህናውን በመጠራጠሩ በድጋሚ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስጭኖ በማምጣት ለሸጡለት ግለሰቦች ከመለሰ በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ተጠርጣሪዎቹ ሊያዙ ችለዋል ተብሏል፡ ፡
ወቅትና አጋጣሚዎችን እየጠበቁ በአቋራጭ ለመክበር በማሰብ ደረጃቸውን ያልጠበቁ እና የሰው ልጅ ጤናን ሊጎዱ የሚችሉ ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡