News

አዲስ ነገር – ለታዳጊ አገራት የቀረጥ ነፃ እድል

ብሪታንያ ከአፍሪካ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመመስረት በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ የታዳጊ ሀገራት ምርቶችን ከቀረጥ ነፃ ለመቀበል መወሰኗ ተሰምቷል፡፡ከመጪው የፈረንጆች አመት መጀመሪያ ላይ እንደሚተገበር በታለመው እቅድ ከሆነ ከምግብ እስከ ጨርቃጨርቅ ያሉ የታዳጊ አገራት ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ ብሪታንያ ይገባሉ፡፡“ለታዳጊ አገራት የቀረጥ ነፃ እድል” በተሰኘው በዚህ መርሃ ግብር መሰረት 99 ከመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ምርት ከቀረጥ ነፃ ወደ ብሪታንያ እንደሚገባ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡የብሪታንያ መንግስት እንደሚለው እቅዱ የብሪታንያን ከአውሮፓ ህብረት መውጣት ተከትሎ ታዳጊ አገራት ከእርዳታ ይልቅ ጠንካራ የንግድ ግንኙነት እንዲኖራቸው የነደፈውን ፖሊሲ የሚተገብርበት ነው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New