News

አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

🇷🇺#ሩሲያ
ቻይና እና ሩሲያ ሁሉን አቀፍ የዓለም ሥርአት ለመመሰረት ቁርጠኛ አቋም መያዛቸውን ይፋ አደረጉ ።
በሩሲያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዩ ከሩሲያ አቻቸው ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወደ አንድ ያጋደለ የዓለም ጎራን እንደሚኮንኑ እና ሁሉንም አገራት የሚያሳትፍ ስርአት ለመመስረት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዩ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ።
🇱🇾#ሊቢያ
የአፍሪካ ሕብረት በጦርነት በደቀቀችው ሊቢያ ላሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የእርቀ ሰላም ጉባኤ ሊያሰናዳ መሆኑን አስታወቀ።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር መሃማት ሙሳ ፋቂ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን የእርቅ ጉባኤ እንዲያስተባብሩ የቀድሞው የኮንጐ ፕሬዚዳንት ዲኒስ ሳሶ ኑጌሶ ተሾመዋል ማለታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል ።
🇸🇴#ሶማሊያ
በሶማሊያ አሸባሪው አልሸባብ በፈፀመው ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ ።
በሶማሊያ ርዕሰ ከተማ ሞቃዲሾ የሶማሊያ እንደራሲዎች መኖሪያ አቅራቢያ ባለ አንድ አፓርታማ የአልሸባብ ታጣቂዎች በፈጸሙት በመኪና ላይ የተጠመደ የቦምብ ፍንዳታ 10 ሰዎች መገደላቸው ነው የተሰማው ።
የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የህዝብ ተወካዮች መኖሪያን ጥሰው በመግባት ጥቃት ያካሄዱ 4 የአልሸባብ አሸባሪዎች በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ ተገድለዋል።
የሃገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የአሸባሪው አልሸባብ በፈፀመው ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ 4 ወታደሮች እና ሌሎች 3 ንፁሃን ዜጎች ለጉዳት መደረጋቸውን የዘገበው ሬውተርስ ነው ።
🇨🇩#ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
ምዕራባዊያኑ አገራት በምስራቅ ኮንጎው ግጭት እጃቸው አለበት ባሉዋቸው የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የሩዋንዳ ወታደራዊ አዛዦች ላይ ማዕቀብ ሊጥሉ ነው ተባለ ።
አሜሪካ ፣ ብሪታንያ እና የአውሮፓ ሕብረት ከሩዋንዳ እና ዴሞክሪቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ ሹማምንት በተጨማሪ በኤም 23 ታጣቂ ቡድን እና የአሸባሪው አይ ኤስ ኤስ አፍቃሪ በሆነው የኢዲኤፍ ቡድን ላይም ብርቱ ማዕቀብ ሊጥሉ መዘጋጀታቸው ነው የተነገረው ።
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በመንግስት ሀይሎች እና በኤም 23 ታጣቂ ቡድን የተከሰተው ግጭት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ ተዘግቧል።
የምስራቅ ኮንጎው ግጭትን ለማቆም በምስራቅ አፍሪካ አገራት አሸማጋይነት የተካሄደው የሰላም ድርድር ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New