News

አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

🇺🇸#አሜሪካ የሜታ ኩባንያ የአሜሪካ ዜና ዘገባዎችን ከማህበራዊ ትስስር ገፁ ፌስቡክ ሊያስወግድ እንደሚችል አስጠነቀቀ።ፌስቡክ የዜና ዘገባዎችን ከትስስር ገፁ ሊያነሳ እንደሚችል ያስጠነቀቀው የዜና አውታሮች ከሜታ ኩባንያ ክፍያ እንዲፈፀምላቸው የሚያስገድድ ረቂቅ ህግ በአሜሪካ ኮንግረስ እየረቀቀ መሆኑን ተከትሎ ነው ።የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን በፌስ ቡክ በሚያሰራጩት ዜናዎች የሜታ ኩባንያ ከፍተኛ ትርፍ እያገኘ ነው በሚል የሚያቀርቡትን ወቀሳ የሜታ ኩባንያ ማስተባበሉን ቢቢሲ ዘግቧል ።

🇷🇺#ሩሲያሩስያ ወደ አውሮፓ የምትልከው የነዳጅ ዘይት ምርት በእጅጉ መቀነሱ ተገለፀ።ሩሲያ ወደ አውሮፓ የምትልከው የነዳጅ ዘይት የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በ5 እጥፍ ሲቀንስ ክሬምሊን በአውሮፓ ፋንታ ወደ ቻይና ፣ ህንድ እና ቱርክ አገራት እየላከች መሆኑ ነው የተነገረው ።ምዕራባዊያኑ በሩሲያ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዘይት የዋጋ ተመን ተከትሎ በቀጣይ ሩሲያ ወደ አውሮፓ የምትልከው የነዳጅ ዘይት ምርት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አር ቲ ዘግቧል ።

🇿🇦#ደቡብ አፍሪካ አጣብቂኝ ውስጥ በወደቁት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ዙሪያ የአገሪቱ ፓርላማ የሚሰጠውን ድምፅ በ 1 ሳምንት አራዝሟል።የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ አፈጉባኤ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩትን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጉዳይ አስመልክቶ ፓርላማው ከ 7 ቀናት በኋላ ድምፅ በመስጠት ውሳኔ ያሳልፋል ብለዋል ።በፕሬዝዳንቱ ላይ ክስ ለመመስረት ከደቡብ አፍሪካ ፓርላማ አባላት ሁለት ሦስተኞቹ የውሳኔ ሐሳቡን ሊደግፉ እንደሚገባ ፍራንስ ቱዌንቲ ፎር ዘግቧል ።

🇸🇴#ሶማሊያ የሶማሊያ መንግስት ወታደሮች አንድ ቁልፍ ከተማን ከአሸባሪው አልሸባብ ማስለቀቃቸውን አስታወቁ ።የሶማሊያ መከላከያ ኃይል ከመዲናዋ ሞቃዲሾ 220 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትነገኘውን አደን ያባል ከተማን ከአልሸባብ ተጣቂዎች ነጻ ማድረጉ ነው የተነገረው።አልሸባብ የአዳን ያባል ከተማን ላለፉት 10 አመታት በቁጥጥር ስር አውሏት እንደነበር ዘኢስት አፍሪካን ዘግቧል ።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New