News

አዲስ ነገር – ኦላ ኢነርጂ

ኦይል ሊቢያ ኢትዮጵያ ሊሚትድ በነዳጅ ማደያ አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በሚገነቡ የመኪና ጥገና ማእከላት ስራ ለመጀመር ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ አለ፡፡
ድርጅቱ ራሱን በአዲስ መልክ በአዲስ ብራንድ በማስተዋወቅ ኦይል ሊቢያ የነበረውን ስያሜ ኦላ ኢነርጂ በሚል መቀየሩንም ያስታወቀ ሲሆን በኦላ ኢነርጂ ስር አዳዲስ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ለየት ያለ ነው ያለውን የደንበኛ አያያዝ ስርአትን ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አዲሱ የድርጅቱ ብራንድ በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ በተመረጡ የነዳጅ ማደያና አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚተገብር ሰምተናል፡፡
ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ሊሚትድ በሃገራችን የመጀመሪያ ነው የተባለለትን የፕሪሚየም የመኪና ጥገና ማእከላቱን እንዲያስተዳድርለት ከጊጋር ትሬዲንግና ቴክኒካል ሴንተር ጋር የሽርክና አጋርነት ስምምነት መፈራረሙ አዲሱን ብራንድ ባስተዋወቀበት መድረክ ተናግሯል፡፡
ድርጅቱ በመስቀል አደባባይ የነዳጅ ማደያና አገልግሎት መስጫ ጣቢያ በሚገኘው አክሰስ አውቶ ኬር ማእከል አዲሱን አገልግሎቱን የማስተዋወቅ መርሃግብር ያከናወነ ሲሆን የመኪና ጥገና ማእከል አገልግሎቱንም ለጎብኚ ደንበኞቹ ክፍት ማደረጉን አስታውቋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New