አዲስ ነገር – የመልሶ ግንባታ ድጋፍ ጥሪ
በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ያደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት ዳያስፖራው እገዛ እንዲያደርግ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪውን ያቀረቡት በኢንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በለንደን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ጋር ባካሄዱት ውይይት ላይ ነው፡፡
በሁሉም የትምህርት እርከን እየተካሄደ ያለው ማሻሻያ ለመጪው የኢትዮጵያ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ መሰረት የሚጥል ነው ሲሉ የተናገሩት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዳያስፖራ ባለሙያዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
አክለውም የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ለሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውን በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማህበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New