አዲስ ነገር – የወንጀል ተጠርጣሪዎች
ሰሞኑን በተካሄደ የሕግ ማስከበር ዘመቻ በተለያዩ ወንጀሎች በህግ ስር ከዋሉት ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ውሳኔ ተላልፎባቸው የነበሩ እንደሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ሁለት መቶ አስሩ በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡
ክልሉ አስተማማኝ ሰላም ላይ ይገኛል ያለው ቢሮው አሁን ላይ ክልሉ ሕገ ወጦች ናቸው በሚል የጠረጠራቸውን ለመያዝ እየሰራ መሆኑን በማመልከት ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ የተለያዩ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት አይታገሳቸውም ብሏል፡፡
እንዲሁም ትክክለኛ የፋኖ አባላትን በመንግሥት መዋቅር ሥር በማድረግ እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑን ተነግሯል፡፡ ዘገባው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New