News

አዲስ ነገር – የመኪና ማቆሚያ ቦታ አጠቃቀም

በአዲስ አበባ የህንጻ ውስጥ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አጠቃቀም ላይ በተደረገ ኦዲት ስልሳ በመቶ የሚሆኑ ህንጻዎች ባልተገባ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አጠቃቀም ምክንያት እርምጃ እንዲወሰድባቸው እና የንግድ ፈቃዳቸው እንዲታገድ ሊደረግ ነው ተብሏል፡፡
ይህንን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፤ በበጀት ዓመቱ ባጠቃላይ በ1 ሺህ 360 ህንጻዎች ላይ የህንጻ ውስጥ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አጠቃቀም ኦዲት ማድረጉን ያስታወቀ ሲሆን በርካታ ህንጻዎች የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን በአግባቡ እየተጠቀሙ እንዳልሆኑ አስታውቋል፡፡
በዋና ማዕከሉ ብቻ ምልከታ ከተደረገባቸው 260 ህንጻዎች መካከል 58 ህንጻዎች የመኪና ማቆሚያን በከፊል ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ሲሆን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ 35 የሚሆኑ ህንጻዎች ማስተካከያ ማድረግ መቻላቸውም ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ቀሪ 23 ህናጻዎች ደግሞ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ማስተካከል ባለመቻላቸው እርምጃ እንዲወሰድባቸው እና የንግድ ፈቃዳቸው እንዲታገድ ለሚመለከተው ቢሮ መላኩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
እንዲሁም በክፍለ ከተሞች ደረጃ ከ1 ሺህ 100 በላይ ህንጻዎች የመኪና ማቆሚያ ቦታ አጠቃቀም ኦዲት እንደተደረገላቸው ቢሮው በመግለጫው የጠቆመ ቢሆንም እንኳ ስለ ዝርዝር ውጤቱ ያለው ነገር የለም፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New