News

አዲስ ነገር – የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሱዳን የቀጠለውን ግጭት ተከትሎ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ረሀብ ሊጋለጡ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሱዳን የቀጠለውን ግጭት ተከትሎ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ረሀብ ሊጋለጡ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል፡፡
ተቋሙ እንደሚለው አሁን ለረሀብ ከተጋለጡት 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሱዳናዊያን በተጨማሪ በመላ ሀገሪቱ ከ 19 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት ይጋለጣሉ ተብሎ ነው የተተነበየው፡፡
ድርጅቱ በሱዳን ለሚያካሄደው የረድኤት ሥራ ከለጋሽ አገራት 3 መቶ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መጠየቁንም ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ የሱዳን ተፈላሚ ኃይሎች የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን ጥሰዋል ሲሉ ከሰዋል።
ምንጩ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የዜና መግለጫ ነው፡፡
🇹🇷#ቱርክ
የረጅም ጊዜ ባላንጣዎቹ ቱርክ እና ሶሪያ ዲፕሎማስያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ ከስምምነት መድረሳቸው ተሰማ፡፡
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና የኢራኑ አቻቸው ሁሴን አሚር አብዶላሄን በሩሲያ መዲና ሞስኮ ባካሄዱት የሽምግልና ጥረት ነው ከ12 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቱርክ እና ሶሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል መስማማታቸው የተነገረው፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአንካራ እና የደማስቆ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የደረሱትን ስምምነት ተፈጻሚ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የሩሲያ እና የኢራን ባለሥልጣናት ባሉበት ቀጣይ ውይይት እንደሚያደርጉ አስታውቋል፡፡
በሶሪያ ጦርነት ቱርክ ታጣቂዎችን በመደገፍ የሶሪያው ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድን ከመንበረ ሥልጣናቸው ለመገልበጥ ለአመታት ስትሰራ እንደነበር ተነግሯል፡፡
ዘገባው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው።
🇸🇦#ሳዑዲ አረቢያ
ሳዑዲ አረቢያ እና ሶሪያ በየሀገራቸው ተዘግተው የነበሩ ኤምባሲዎቻቸውን መልሰው ለመክፈት ከስምምነት መድረሳቸውን ይፋ አደረጉ።
የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሶሪያ ደማስቆ የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ እንዲከፈት መወሰኑን ሲያስታወቅ የሶሪያ መንግሥት በበኩሉ ለ11 አመታት ተዘግቶ የቆየውን በሶሪያ የሪያድ ኤምባሲ ሥራ እንደሚጀምር ገልጿል፡፡
የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ የሚከፈተው የሀገሪቱ ኤምባሲ በሁለቱ የአረብ ሀገራት መካከል ያለውን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ እንደሆነ አስታውቋል።
ዘገባው የአሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡
🇨🇩#ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በደረሰ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 410 መድረሱ ተገለፀ ።
በሀገሪቱ ኪቩ በተባለ ግዛት ከቀናት በፊት ባጋጠመው የጐርፍ አደጋ ይሄ ዘገባ እስከተጠናከረበት ድረስ ብቻ 410 ሰዎች ሲሞቱ 5ሺ 5 መቶ የሚሆኑ ዜጐች የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል ።
የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን አንድ ኃላፊ የጐርፍ አደጋው በጋጠመበት ኪቩ ግዛት በተለይ ኒያኩምቢ የተባለ አካባቢ ሙሉ ለሙሉ በጐርፍ መጥለቅለቁ እና በርካታ መኖሪያ ቤቶች መስጠማቸውን ገልጠዋል።
ዘገባው የአር ቲ ነው፡፡
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New