EthiopiaNews

ኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የመጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች ፦

🔸ኢትዮጵያ በኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ 2026 ፎረም ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ህንድ፣ ሲንጋፖርና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሟን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

🔸ከነገ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ተጓዦች የቪዛ ዋስትና ገንዘብ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል።

🔸የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ በስምንት ወራት ውስጥ ከ2.6 ሚሊዮን በላይ የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች መሰጠት መቻሉን ተናገሩ።

🔸የኢትዮጵያ አየርመንገድ ከአፍሪካ አቪየሽን ማህበር ጋር ያሰናዳው የአፍሪካ የአቪየሽን ጥገናና እድሳት ጉባኤ በአዲስአበባ ተካሂዶ ተጠናቋል ፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews