LatestNews

ኢትዮጵያ ከቡና ምርት ከ130 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን ገለፀች፡

ኢትዮጵያ በግንቦት ወር 2013 ዓ.ም ወደ ውጭ አገራት ከላከችው 32 ሺህ 669 ቶን የቡና ምርት ከ130 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ መገለጹን እናገኛለን፡፡የቡናና ሻይ ባለስልጣን ለአዲስ ነገር በላከው መግለጫ ላይ እንደተመለከተው በመጋቢት ወር አገራችን ለአለም ገበያ ካቀረበችው 27 ሺህ 200 ቶን የቡና ምርት 107 ሚሊየን ዶላር ተገኝቶ የነበረ ሲሆን በሚያዝያ ወር ደግሞ ከ28 ሺህ ቶን በላይ ቡና ተልኮ 114 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተመዝግቧልም፡፡ታዲያ በግንቦት ወር ተገኘ የተባለው ገቢ እስከ ዛሬ ድረስ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ለአለም ገበያ ከተላከው ቡና የተገኘ ከፍ ያለ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ስለመሆኑ ነው ከመግለጫው የተመለከትነው፡፡የዘንድሮው ገቢም አምና በአንድ ቶን ይገኝ ከነበረው 3 ሺህ 700 ዶላር እስከ 4 ሺህ ዶላር ድረስ ጭማሪ የታየበት መሆኑን የቡናና ሻይ ባለስልጣን በመግለጫው ጨምሮ ገልጿል፡፡

#አዲስነገር #WhatsNew