ኢትዮጵያ የተቀበለችው ሃላፊነት
ኢትዮጵያ የሚያዝያ ወር 2018 ዓ.ም የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነት ቦታ መረከቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ የምክር ቤቱን አጀንዳዎች የመምራት ስራዋን በይፋ የምትጀምረው በመጪው መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን በዚህ ቆይታዋ የተለያዩ አህጉራዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮችን፣ የሀገራት ሁኔታዎችና የተለያዩ አጀንዳዎችን በሚመለከቱ ውይይቶች ላይ አመራር ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ በአውሮፓውያኑ በ2004 ከተመሰረተ ጀምሮ ኢትዮጵያ ለአራት የሥራ ዘመናት በምክር ቤቱ ውስጥ አገልግላለች።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
