EthiopiaNews

እርምጃ በሕገ ወጥ ንግድ ድርጅቶች ላይ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አላግባብ ሲሰሩ የተገኙ 11,811 ድርጅቶች በሕግ እንዲጠየቁ ማድረጉን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ትናንት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረበው የ 8ወራት ሪፖርቱ ላይ ነው።

ሚኒስቴሩ ባደረገው የቁጥጥር ስራ በአግባቡ አልሰሩም በተባሉ በ345,462 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ለ171,059 ድርጅቶች የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣በ21,743 ድርጅቶች ላይ የንግድ ስራ ፈቃድ እገዳ ፣11,811 በህግ እንዲጠየቁ እና በ1,157 ድርጅቶች ላይ የንግድ ስራ ፈቃድ ስረዛ እርምጃዎች ተወስዷል ብሏል።

መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews