LatestNews

ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው ተብሏል፡፡

ከዓለም ባንክ በተገኘ ከ24 ሚሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው ተብሏል፡፡ የማዕከሉ ግንባታ የስልጠና ተደራሽነትን የማስፋት፣ የትምህርትና ሥልጠና ጥራትን የማሻሻል እንዲሁም ቀጠናዊ ትስስርን የማጠናከር አላማዎችን ያነገበ ነው የተባለ ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ አገራትን በትምህርትና ስልጠና የሚያስተሳስር እንደሚሆንም ተነግሮለታል። የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚንስትሩ ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ለማዕከሉ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት ማዕከሉ በብረታ ብረት እንዲሁም በቆዳና የቆዳ ውጤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል። ዘገባው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision