EthiopiaNews

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ገቢ

የአለም ባንክ በፈረንጆቹ 2024/25 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ መንግስት የልማት ድርጅቶች 117 ቢሊየን ብር ለመንግስት በጀት መመደብ መቻላቸውን አስታወቀ።

ባንኩ በዚሁ በጀት ዓመት የመንግስት የልማት ድርጅቶች 98 ቢሊየን ብር ግብር እና 19 ቢሊየን ብር ትርፍ ለመንግስት መክፈላቸውን ባወጣው መረጃ ገልጿል።

ባንኩ ጨምሮም የመንግስት የልማት ድርጅቶቹ ከነበሩባቸው የእዳ ጫና ወጥተው የመንግስት ስራ የመፍጠር አጀንዳን እየደገፉ ነው ብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN