EthiopiaNews

የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነትና አፍሪካ

የአፍሪካ ልማት ባንክ የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ለሦስት ወራት ከቀጠለ የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ዜሮ ነጥብ ሁለት በመቶ እንዲሁም ለስድስት ወራት ከቀጠለ ደግሞ የኢኮኖሚ እድገቱም በ1 ነጥብ 5 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ገለጸ፡፡

ጦርነቱ ባስከተለው የዋጋ ግሽበት ተጽዕኖ ሳቢያ የ29 የአፍሪካ አገራት ገንዘብ የመግዛት አቅም ማሽቆልቆሉን የጠቀሰው ባንኩ ጦርነቱ የነዳጅ፣ የምግብና ማዳበሪያ ዋጋ እንዲያሻቅብ ማድረጉ ከወዲሁ በርካታ አገራትን እየፈተነ ይገኛል ብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት በበኩሉ በጦርነት ምክንያት በዓለም ዙሪያ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ መጨመሩን ያስታወቀ ሲሆን ባወጣው የምግብ ሸቀጦች ዋጋ አመልካች ዝርዝር ላይ በየካቲትና በመጋቢት ወራት የ2 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ መታየቱን ገልጿል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews