EthiopiaNews

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የነበራት የረጅም ጊዜ የነዳጅ ግብይት ውል በጦርነቱ ምክንያት መስተጓጎሉንና አቅራቢ ሀገራቱ ምርቱን ማቅረብ የማይችሉበት ሁኔታ መፈጠሩን ተናገሩ።

ሚኒስትሩ በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎች መተላለፋቸውንም አሳውቀዋል።

በጦርነቱ ምክንያት በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ አለመቅረቡን ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል።

በጦርነቱና አለመረጋጋቱ ምክንያት በነጭ ናፍጣ ላይ የነበረው የቀን አቅርቦት ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ማለቱንም አክለዋል።

መረጃው ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews