የማይክሮ ፋይናንስ ትርፍ
የኢትዮጵያ ማይክሮ ፋይናንስ ዘርፍ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2024/25 በጀት ዓመት ከፍተኛ ትርፍ ማስመዝገቡን ፋይናንስ ኢን አፍሪካ ባወጣው ግምገማው ገልጿል።
በግምገማውም የሃገሪቱ ማይክሮ ፋይናንስ ዘርፍ የተጣራ ገቢ ወደ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ22 ነጥብ 6 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።
በዚህም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ቁጥር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ56 ወደ 1 ሺህ 200 በላይ ቅርንጫፎች ከፍ ማለቱ በግምገማው ተገልጿል።
እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ በ33 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 41 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የብድር መጠኑም ወደ 48 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱን በፋይናንስ ኢን አፍሪካ የተገመገመ መረጃ ያሳያል።
ይህ ዕድገት በተቀማጭ ገንዘብ መጨመር፣ በካፒታል ማቆያና የተሻሻለ የንብረት ጥራት የተገኘ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የገንዘብ አቅርቦቶች አለመመጣጠንና የውጤታማነት ጉድለቶች ደግሞ እንደችግር ተነስተዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
