InternationalNews

የሩሲያ ቀድመ ሁኔታ

🔸ሩሲያ የዩክሬን ወታደሮች ግዛቴ ነው ከምትለው የዶንባስ ግዛት በሁለት ወራት ዕድሜ ለቀው እንዲወጡ ቀነ ገደብ ማስቀመጧን ፕሪዚዳንት ዜለንስኪ ተናገሩ።

🔸የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ይህን ያሉት በአካባቢው ጦርነት ላይ ዛሬ ከአሜሪካ ጋር ድርድር ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ ነው፡፡

🔸ዜሌንስኪ በአገራቸው በሩሲያና አሜሪካ መካከል በአሁኑ ንግግር የድንበር ጉዳይ ተነስቶ አንዳች ስምምነት ይደረሳል ተብሎ ሲጠበቅ ሞስኮ ይህን ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧ ተገቢ አይደለም ሲሉ ተችተዋል፡፡

🔸ኪዬቭ ጦርነቱ አሁን በተያዙት ድንበሮች ላይ ቆሞ ንግግር እንዲደረግ ብትፈልግም ሞስኮ ግን በመጭዎቹ ሁለት ወራት የዶንባስ ግዛትን ሙሉ በሙሉ ነጻ ለማውጣት መዘጋጀቷን ለአሜሪካ እንደነገረች እየተዘገበ ነው፡፡

🔸ዜሌንስኪ ቀደም ብለውም አሜሪካ ዶንባስን ለቀን እንድንወጣ ጫና እያደረገችብን ነው ያሉ ሲሆን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የዜሌንስኪን አባባል ፍጹም ሃሰት ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews