EthiopiaNews

የሰሞኑ ከባድ ዝናብ

በቀጣዮቹ 11 ቀናት ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ሊያስከትል የሚችል ከበድ ያለ ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታውቋል።
በተለይም በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንካራ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር ነው ኢኒስቲትዩቱ የገለጸው።

በተጨማሪም በፀሐይ ኃይል ታግዞ ከሚፈጠረው ጠንካራ የደመና ክምችት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅና በመካከለኛው የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ በረዶና ነጎድጓድ የቀላቀለ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል ብሏል።
ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ሊያጋጥም ስለሚችል የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡