EthiopiaNews

የባንኩ የጥንቃቄ መልዕክት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘመኑ የዲጂታል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የግለሰቦች ስልክ እንደ ባንክ ሂሳብ እያገለገለ እንደሚገኝ ጠቅሶ ደንበኞች በጥንቃቄ ጉድለት ገንዘባቸውን እንዳይዘረፉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ሚስጥራዊ ቁጥሮችን ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት ለማጭበርበር ወንጀሉ ዋነኛው መንገድ ነው ያለው ባንኩ ደንበኞች ሊገነዘቧቸው ይገባል ያላቸውን የጥንቃቄ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት ማንኛውም ደንበኝ የባንክ ሂሳብ ቁጥሩን እና የሞባይል ባንኪንግ የይለፍ ቃሉን ለማንኛውም አካል አሳልፎ መስጠት እንደማይገባ እና በቀላሉ የማይገመቱ የይለፍ ቃላትን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ገልጿል።

በተያያዘም ባንኩ ለደንበኞች በስልክ ደውሎ ሚስጥራዊ ቁጥር የሚጠይቅበት አሰራር እንደሌለ ጠቅሶ ደንበኞች በማይታወቁ አካላት የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎችን እንዳይከፍቱም አስጠንቅቋል።

ባንኩ በዚሁ መግለጫው ደንበኞች ስልካቸውን ለጥገናም ሆነ ለሌላ ጉዳይ ለሰው ሰጥተው ሲቀበሉ አጠራጣሪ መተግበሪያዎች አለመጫናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቦ የጥንቃቄ መልዕክቱ የወጣው በዲጂታል የክፍያ አማራጮች ላይ የሚታዩ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመግታት በማለም መሆኑን ገልጿል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews