የተመዘገቡት መራጮች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ28 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት መመዝገባቸውን አስታወቀ።
ቦርዱ ባወጣው መግለጫ ከየካቲት 28 ቀን ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በዲጅታል እና በማኑዋል አማራጭ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።
የመራጮች ምዝገባ ሂደትን አስመልክቶ ቦርዱ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በድምሩ 28 ሚሊዮን 365 ሺህ 310 መራጮች መመዝገባቸውን ገልጿል።
ለመራጭነት ከተመዘገቡት ዜጎች ውስጥ 13 ሚሊየን 47 ሺህ 743 ሴቶች ሲሆኑ፤ 15 ሚሊየን 317 ሺህ 567 ደግሞ ወንዶች ናቸው።
መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
