EthiopiaNews

የነዳጅ ስርጭት ድልድል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በነዳጅ ማዲያዎች ቅድሚያ አገልግሎት የሚያገኙ ተቋማትን ይፋ አደረገ ።

ቢሮዉ በመካከለኛ ምስራቅ በተከሰተዉ ቀዉስ ምክንያት የተፈጠረዉን የነዳጅ እጥረት ለመከላከል በነዳጅ ማዲያዎች ቅድሚያ አገልግሎት የሚያገኙ ተቋማትን ይፋ አደርጓል፡:

በዚህም መሰረት፤-

👉ለነዳጅ አጓጓዥ ተሽከርካሪዎች/ ቦቴዎች፤

👉ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች፤መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ ምርቶች እና የኤክስፖርት ምርቶችን የሚያመርቱ፤

👉ግንባታ ላይ ላሉና ትኩረት ለሚሰጣቸዉ የመንግስትና ግል ፕሮጀክቶች፤

👉ለደረቅ ጭነት እና ለግንባታ ቁሳቁስ አጓጓዥ ተሽከርካሪዎች (ገበያ ለማረጋጋት የግበንርናና ኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶች የሚጓዙ ተከርክርካሪዎች ይጨምራል)

👉ለግብርና ማሽነሪዎች / ትራክተሮች

👉ለሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች

👉ለከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች

👉ለሕብረተሰብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ( አምቡላንስ፡ ቀዶ ጥገና የሚሰሩ ተቋማት፡ መብራትና

👉ሌሎች እንደአስፈላጊነቱ በንግድ ቢሮ እየቀረበ በግብረ ሃይል እየታየ ዉሳኔ ሲሰጥ የሚጨመር መሆኑን ቢሮዉ ገልጿል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews