EthiopiaNews

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከመጋቢት 23 ቀን 2018 አ.ም ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ መሰረት በሊትር፦-

-ነጭ ናፍጣ 163.09 ብር
-ቤንዚን 142.41 ብር
– ኬሮሲን 151.39 ብር
– ቀላል ጥቁር ናፍጣ 163.98 ብር
– ከባድ ጥቁር ናፍጣ 160.68 ብር
– የአውሮፕላን ነዳጅ 150.48 ብር ሆኗል።

የቀጥታ ተጠቃሚዎች የነጭ ናፍጣ መሸጫ ዋጋ ደግሞ 210 ብር መደረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ መንግስት አሁንም ቢሆን በአንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ ላይ 71 ብር እንዲሁም በቤንዚን ላይ 32 ብር ድጎማ እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ወደ ኢትዮጵያ ይገባ የነበረ 120 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ እና 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅ የጫኑ ሶስት መርከቦች በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ቆመው እንደሚገኙ ገልጿል።

መንግስት የነዳጅ መደበኛ አቅርቦቱ እንዳይቋረጥ ከተባራሪ ገበያ በከፍተኛ ዋጋ በመግዛት ለማቅረብ ጥረት እያደረገ ይገኛል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች ከመጋቢት 23 ጀምሮ ከመንግስት በደረሳቸው ደብዳቤ መሰረት በአዲሱ ዋጋ ሲሸጡ እንደነበር ተገልጿል።

መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews