EthiopiaNews

የአሜሪካ አምባሳደር መልዕክት

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በኢትዮጵያ የቆይታ ጊዜያቸው በማለፉ ምክንያት የቅጣት ክፍያ እየተከማቸባቸው የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ ዜጎች መንግስት ባቀረበው በጊዜ የተገደበ ዕድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቀረቡ፡፡

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ ዜጎች ወደ ሕጋዊ አሰራር እንዲገቡ ዕድል መስጠቱን ያነሱት አምባሳደሩ ይህ ዕድል እስከ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ብቻ የሚቆይ መሆኑን በመጥቀስ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

በዚህ ጊዜ ውስጥ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ቅጣታቸው ሙሉ በሙሉ ተሰርዞላቸው እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ አዋቂዎች ደግሞ ከቅጣት ክፍያው ግማሽ የሚሆነውን በመክፈል የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቅያ ካርድ ወይም “ቢጫ ካርድ” ማግኘት እንደሚችሉም አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

ከግንቦት 15 ቀን በኋላ ከኢትዮጵያ ለመውጣትም ሆነ ለኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቅያ ካርድ ለማመልከት ከተፈቀደ የቪዛ ቆይታ ጊዜ በላይ የመቆየት ቅጣትን መቶ በመቶ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖር በመጥቀስ የኢሚግሬሽን ቅጣት ያለባቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጋጣሚውን እንዲጠቀሙም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews