የአሜሪካ ጦር ዝግጅት
አሜሪካ ኢራን በዚህ ሳምንት እስራኤል ላይ ልትወስድ ትችላለች ላለችው የበቀል እርምጃ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጓን ገልፃለች።
የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት መስሪያ ቤት ሃላፊ ጆን ኪርቢ ለኤቢሲ ዘጋቢዎች እንደተናገሩት ኢራን በህዚ ሳምንት መጀመሪያ እስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ ልትወስድ ትችላለች የሚለው የአሜሪካ ግምገማ ከእስራኤል ግምገማ ጋር መግጠሙን ተናግረዋል።
አሜሪካ የላከችው የጦር አውሮፕላን ጫኝ መርከብ በመካከለኛው ምስራቅ መድረሱን እና ሚሳኤል ተሸካሚ ባህር ሰርጓጅ መርከብ ደግሞ ወደ ስፍራው መላኩን አስታውሶ የዘገበው ኤቢሲ ኒውስ ነው።