የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 50 በመቶ የሚሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከንቲባዋ አክለውም የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ፣ ፈጣንና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ የተጀመረው ስልታዊ እንቅስቃሴ ነዋሪዎች የንግድ ፈቃድ ማደስን፣ ግብር ማሳወቅንና የግንባታ ፈቃድ ማግኘትን የመሰሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ወይም ከሥራ ቦታቸው ሆነው በኮምፒውተርና በሞባይል እንዲያከናውኑ አስችሏቸዋል ብለዋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የተጀመረው የ“መሶብ” ዲጂታል አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ወደ 6 ማዕከላት ማሳደግ መቻሉንና አገልግሎቱን ካገኙ 130 ሺህ ነዋሪዎች መካከል 98 በመቶ የሚሆኑት በተደረገላቸው መስተንግዶ መርካታቸውን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ ጨመረውም በቀጣይ አንድ ወር ውስጥም በቀሪዎቹ 5 ክፍለ ከተሞች ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎት መስጫ ሕንጻዎች ተጠናቅቀው ወደ ሥራ ሲገቡ፣ መላው አዲስ አበባ በዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደምትሸፈን ይጠበቃል ነው ያሉት።
በሥራ ብዛት ወደ ቢሮ መምጣት ለማይችሉ ነዋሪዎች ምቾት ሲባል ደግሞ በዘመናዊ አውቶቡሶች ላይ የተገጠሙ “ተንቀሳቃሽ የዲጂታል አገልግሎት መስጫዎች” በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምሩ ከንቲባዋ አሳውቀዋል።
የተገልጋዩን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ከመቆጠቡ ባለፈ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን ትስስር እንደሚያጠናክር የተገለጹት ከንቲባዋ በቀጣይ5 ዓመታት ውስጥ አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ በስማርት አገልግሎቶች ለማዳረስ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
