EthiopiaNews

የትንሣኤ በዓል

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የ2018 ዓ/ም የትንሣኤ በዓል በሰላም መከበሩን  አስታወቀ።

ፖሊስ ትናንት በቦሌ ክፍለ ከተማ ካጋጠመ ድንገተኛ የሞት አደጋ ውጭ የተለየ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ በበዓሉ ዋዜማ ሆነ በበዓሉ እለት አላጋጠመም ሲል ገልጿል።

ሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጆኒ ጋራዥ አካባቢ ጠዋት ላይ የ59 ዓመት ግለሰብ በበሬ ተወግተው ህይወታቸው ማለፉን ፤ በሌላ ሰው ላይም ጉዳት መድረሱን ገልጿል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews