Sports

የአውሮፖ ክለቦች ዝውውር

የአውሮፖ ሊጎች ሊጀመሩ መቃረባቸውን ተከትሎ ቡድኖች ክፍተቶቻቸውን ለመሙላት ከጊዜ ጋር ሩጫ ጀምረዋል። በዚህም የጀርመኑ ክለብ ባየርሙኒክ ሆላንዳዊውን ተከላካይ ማቲያስ ዲላይትን በይፋ አሰፈርሟል።የባቫሪያኑ ክለብ የ22 አመቱን ተከላካይ የግሉ ለማድረግ በቅድሚያ 70 ሚሊዮን ዩሮ የከፈለ ሲሆን አቋሙ እየታየ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ዩሮ ለጁቬንቱስ ለመክፈልም ተስማምቷል ። ማቲያስ ዲላይትም በአልያንዝ አሬና እስከ 2027 የሚያቆየውን የ5 አመት ውል ፈርሟል።

በሌላ በኩል ሆላንዳዊውን ተከላካይ ያጣው ጁቬንቱስ ብራዚላዊውን የቶሪኖ ተከላካይ ጌልሰን ብሬመርን ተተኪው አድርጓል ። አሮጊቷ በኢንተር ሚላን በጥብቅ ሲፈለግ የነበረውን የ25 አመቱን ተከላካይ ለማስፈረምም 41 ሚሊዮን ዩሮ በቅድሚያ የከፈለች ሲሆን ተጨዋቹም ለአምስት አመታት በቱሪኑ ክለብ የሚቆይ ይሆናል።ብሬመር ዛሬ ጠዋት የህክምና ምርመራውን ያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በይፋ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል ።በሌላ የዝውውር ዜና ቼልሲ በመጨረሻም የሲቪያውን ተከላካይ ጁሊየስ ኩንዴን ለማስፈረም ከጫፍ መድረሱ ተሰምቷል።

ሰማያዊዎቹ አንቶኒዮ ሩዲገርን እና አንድሬስ ክርስትስንን ማጣታቸውን ተከትሎ የተከላካይ ስፍራቸውን ለማጠናከር እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝ እና ካሊዱ ኩሊባሊን ወደ ቡድናቸው መቀላቀላቸው የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ፈረንሳያዊውን ተከላካይ የግላቸው ለማድረግ ከምንግዜውም በላይ ተቃርበዋል ።ለተጨዋቾቹ ፊርማ ከባርሴሎና ጋር ፉክክር ውስጥ የነበሩት ሰማያዊዎቹ በመጀመሪያ ያቀረቡት የዝውውር ሂሳብ ውድቅ ቢደረግባቸውም በድጋሚ ያቀረቡት 51+4 ሚሊዮን ፓውንድ በሲቪያ ተቀባይነት ማግኘቱ እየተነገረ ይገኛል። ተጨዋቹ በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያ ከቼልሲ ጋር ከተስማማ አመት እንደሆነው ይታወቃል።

የማንቺስተር ሲቲው አሰልጣኘ ፔፕ ጋርዲዮላ ኦሌክሳንደር ዚንቺንኮ ወደ አርሰናል የሚያደርገውን ዝውውር ማጠናቀቁን ይፍ አድርጓል፡፡ መድፈኞቹ ዩክሬናዊውን ተከላካይ ከኢትሃድ ለማስኮብለል 30 ሚሊየን ፓውንድ ለመክፈል መስማማታቸው የሚታውቅ ሲሆን የ25 አመቱ ተከላካይም በትላንትናው ዕለት የመጀመሪያ ዙር የህክምና ምርመራውን ለማድርግ የሲቲን የልምምድ ማዕከል ለቆ መውጣቱ ተነግሯል፡፡

ዌስትሃም ዩናይትድ እና አዲስ አዳጊው ኖቲንግሃም ፎረስት ጄዜ ሊንጋርድን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል ።እንግሊዛዊው ተጫዋች ያለፈውን አመት አጋማሽ በዌስትሃም ማሳለፉን ተከትሎ ወደ መዶሻዎቹ የማምራት ሰፊ ዕድል አለው ቢባልም ኖቲንግሃሞች ዳጎስ ያለ ጥቅማጥቅም በማቅረብ ከተጫዋቹ ተወካዮች ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል ።

የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ ዩሊያን ኔግልስማን የባርሴሎናን ከፍተኛ የዝውውር ተሳተፎ ሸንቆጥ የሚያደርግ አሰተያየት ስጥተዋል ። “የካታላኑ ክለብ የገባበት ከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ የ7 ጊዜ የባላንዶር አሸናፊውን ሊዮኔል ሜሲን ጭምር እንዲያጣ እንዳደረገው የሚታወቅ ሲሆን በዚህ የዝውውር መስኮት አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ ለመቀላቀልም ተጨዋቾችን መሸጥ እንዳለበት ሲነገር ቆይቷል። ሆኖም ከወዲሁ የአንድሬስ ክርሰትሰን ፣ ፍራንክ ኬሲ፣ የራፊንሃ እና የሮበርት ሊዋንዶውስኪን ዝውውር ማጠናቀቁ አነጋጋሪ ሆኗል ። ፖላንዳዊውን አጥቂ በብላግራናዎቹ የተነጠቁት የጀርመኑ ክለብ አሰልጣኝም አውነቱን ለመናገር በአለማችን ምንም አይነት ገንዘብ ሳይኖረው የፈለጋቸውን ተጨዋቾች ሁሉ የሚያስፈርመው ባርሴሎና ብቻ ነው ብለዋል”።አክለውም አንዴት አንደሚያደርጉት አለውቅም የሚገረም እና እብደት የሆነ ነገር ነው ሲሉ ተደምጠዋል ።
ረፖርተር፡ ነቢል መሐመድ

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS