EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢ ክልከላ

🔸የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞቹ በመደበኛ የስራ ሰዓት የግል የእጅ ስልክ እንዳይጠቀሙ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን አስታወቀ፡፡

🔸ከ7 ሺህ በላይ ሰራተኞቹ ጋር ውይይት ማድረጉን የጠቀሰው ቢሮው ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ሰራተኛ በመደበኛ የስራ ሰዓት የግል የእጅ ስልክ መጠቀም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

🔸አገልግሎት ፈላጊን አስቀምጦ በግል የእጅ ስልክ መጠቀምና ለሥራ በተመደበ ኮምፒውተር የግል ጉዳዮችን መከታተል ዋነኛው የአገልግሎት መጓተት ምክንያት ሆኖ መገኘቱን የጠቀሰው ቢሮው አዲሱ መመሪያ የግብር ከፋዮችን እርካታ ለማረጋገጥና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማሻሻል ያለመ መሆኑንም ጠቅሷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews