InternationalNews

የኢራን ማስጠንቀቂያ

🔸የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን እንድትከፍት የሰጡት ቀነ ገደብ እየተጠናቀቀ መምጣቱን ተከትሎ ኢራን ጥቃት ከተፈጸመባት ባላት አቅም ሁሉ ከባድ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች።

🔸ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ነገ የሚጠናቀቅ በመሆኑና ባስተላለፉት መልዕክት ማክሰኞ የኢራን የኃይል መሰረተ ልማትና ድልድዮች የሚወድሙበት ዕለት ነው ሲሉ ዝተዋል፡፡

🔸ለዚህ የፕሬዝዳንቱ ዛቻ ምላሽ የሰጠችው ቴህራን አሜሪካ በሲቪሎች መሰረተ ልማት ላይ ጥቃት ከፈጸመች በቀጠናው ሀገራት መሰረተ ልማቶች ላይ ተመሳሳይ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ገልጻለች፡፡

🔸ሆኖም ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሲቪሎች መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ስለመፈጸም መዛታቸው ተቃውሞ እያስተናገደ የሚገኝ ሲሆን ድርጊቱንም የጦር ወንጀል በሚል እየተጠራ እንደሚገኝ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews