InternationalNews

የኢራን ጦርነት

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የኢራኑ ጦርነት ከግማሽ በላይ ተካሂዷል አሉ።

ኔታንያሁ ጦርነቱ ከግማሽ በላይ ሄዷል ቢሉም ቀሪውን ውጊያ የሚወስነው የሚቀረው ተልዕኮ ነው እንጂ የሚፈጀው ጊዜ አይደለም ብለዋል።

በሌላ በኩል በሚሊዮን በርሜሎች የሚለካ ነዳጅ የጫነች አንዲት የኩዌት መርከብ መልህቋን በጣለችበት ወደብ በኢራን ተመታለች።

መርከቧ ወዲያው በእሳት ስትያያዝ የመርከቧ ሰራተኞች በሰላም ከመርከቧ መውጣታቸው ነው የተገለፀው።

በእስራኤልና በቴህራን ተመሳሳይ ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን ቴህራን ለሊቱን በከፊል የኤሌክትሪክ አገልግሎት አጥታ አድራለች።

የኢራን መንግስት በሆርሙዝ ሰርጥ የሚያልፉ መርከቦች ሁሉ የኮቴ ክፍያ እንዲፈፅሙ በወጠነው ዕቅድ እንደገፋበት የቢቢሲ ዜና አመልክቷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews