የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ መቀነስ
የአለም ባንክ በኢራን ጦርነት ሳቢያ ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት በፈረንጆቹ 2026 አመት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ በሚል ከዚህ ቀደም አውጥቶት የነበረውን የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ቀነሰ።
ባንኩ በጦርነቱ ምክንያት ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት በ2026 አመት ያስመዘግባሉ ተብሎ የተነበየው የ4.4 በመቶ የኢኮኖሚ እድገትን ወደ 4.1 በመቶ ቀንሶታል።
ጦርነቱ የነዳጅና ማዳበሪያ ዋጋን መጨመሩንና በተለይ የባሕረ ሠላጤው አገራት በምስራቅ አፍሪካ ባላቸው የማዕድን፣ የሪል እስቴት እና የታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት ላይ ስጋት መደቀኑ ተገልጿል።
ጦርነቱ ከቀጠለና የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የሠራተኛ ቅጥር ፍላጎት ከቀነሠ፣ ተቀጣሪ አፍሪካዊያን ወደ አገራቸው የሚልኩት ገንዘብ ሊቀንስ እንደሚችልም ባንኩ አሳስቧል። ዘገባው የሮይተርስ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
