EthiopiaNews

የወጪ ንግድ ገቢ

🔸የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ በስምንት ወራት ውስጥ ከ6.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ንግድ ገቢ መገኘቱን ተናገሩ።

🔸ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት ዛሬ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ነው ተብሏል።

🔸ሚኒስትሩ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 5.83 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 6.76 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል።

🔸ሚኒስትሩ የዘንድሮው አፈጻጸም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ50 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል።

🔸በሀገሪቱ የተወሰደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምርትና ምርታማነትን ማሳደጉ፣እና የገበያ መዳረሻዎችን የማስፋት ሥራ መሠራቱ ገቢው እንዲያድግ አድርጓል ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews