News

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ በአሜሪካ መስፋፋት

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ስርጭት በአሜሪካ እድገት በማሳየቱ ለ150 ሺህ ሰው የሚበቃ ተጨማሪ ክትባት በሃገሪቱ ሊሰራጭ ነው።
ባለፈው የፈረንጆቹ ሰኔ ወር ለ56 ሺህ ሰው የሚበቃ ክትባት በሃገሪቱ የተሰራጨ ሲሆን ከዛሬ ማክሰኞ የሚጀመረው ክትባት ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ባለፈ በመደበኛነት ፈንጣጣ ቫይረስን ጨምሮ ለመከላከል የሚያስችል መሆኑም ተነግሯል።
ክትባቱ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው በመስጠት ለሁሉም የማዳረስ ስራ እንደሚሰራም ተነግሯል። ዩ ፒ አይ እንዳለው ቫይረሱ በአሜሪካ ከታየ በኋላ በሃገሪቱ ባሉ 39 ግዛቶች 800 የሚጠጉ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS