EthiopiaNews

ገበያው እንዴት ዋለ?

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን የዲጅታል ቲም በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ገበያው እንዴት ዋለ በማለት በአስኮ፣ዊንጌትና ገርጂ በችርቻሮ የንግድ ዘርፍ ተሰማርተው በሚገኙ ሱቆች ላይ እለታዊ ቅኝት ማድረግ ችለን ነበር። ያነጋገርናቸው የታሸገ ዘይት የችርቻሮ ነጋዴዎች ምንም አይነት የዘይት አቅርቦት እንደሌላቸው ለማወቅ ችለናል።

ህብረተሰቡ በነጋዴዎች ያልተገባ ጭማሪ መማረራቸውን ለጣቢያችን ገልፀው ነጋዴዎች የዘይት ዋጋ ሊጨምር ይችላል በሚል ስጋት እንደደበቁ ነግረውናል። እናንተስ አካባቢያችሁን ጠቅሳችሁ የዘይት አቅርቦት አለ? ካለ ዋጋውስ ስንት ነው?