144 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ ቤት ተሸኙ

44 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ መሸኘታቸውን በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጄኔራል ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ዜጎች በከፋ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ሲሆን ከቤሩት ወደ አዲስ አበባ ተሸኝተዋል፡፡

ትናንት አዲስ አበባ የገቡትን ጨምሮም በሁለት ቀናት ውስጥ 276 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው መሸኘታቸውንም ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

አሁንም በተከታታይ ቀናት ዜጎችን ወደ ሃገራቸው የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከፅህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡