News

25 ነጥብ 9 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ ተባለ

25 ነጥብ 9 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ይሻሉ ተባለ
በኢትዮጵያ ድጋፍ ይሻሉ የተባሉት ዜጎች ሶስት አራተኛ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ በዘጠኙ ክልል ውስጥ ተፈናቅለው ይገኛሉ የተባሉ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎችንም ያጠቃለለ መሆኑ ተገልጿል።
ሪሊፍ ዌብ ኦቻን ጠቅሶ እንደዘገበው በአገሪቱ ከፈረንጆቹ 2022 መባቻ ጀምሮ የተከሰቱት ግጭት፣የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣የሰላም መደፍረስና በቅርቡ በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ያጋጠመው የጎርፍ አደጋ ለድጋፍ ፍላጎቱ መጨመር ምክንያት ናቸው ተብሏል።
ምንም እንኳን በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶች የህይወት አድን እርዳታዎች ቢያደርጉም የነዳጅ እጥረት ግን አሁንም ፈተና መሆኑ ተገልጿል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS