InternationalNews

4 ሺህ የሚደርሱ የእምነት ቦታዎች በሩዋንዳ መንግስት ትእዛዝ እንዲዘጉ መደረጋቸውን  ተነገረ

የሃገሪቱን የጤና እና ደህንነት ደንብ ተላልፈው በመገኘታቸው መዘጋታቸው የተነገረው የሩዋንዳ ቤተ እምነቶች አብዛኛዎቹ ደረጃቸውን ባልጠበቁ፣ የንፅህና ጉድለት ባለባቸው ድንኳን መሳይ መጠለያ ውስጥ የአምልኮ ስርአቶቻቸውን የሚፈፅሙ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።
አሁን ላይ ተፈፃሚ መሆን የጀመረው የሩዋንዳ የሐይማኖት ተቋማትን የተመለከተው ሕግ ከ 5 ዓመታት በፊት መውጣቱ የተነገረ ሲሆን ተቋማቱ እራሳቸውን ለማረም ሰፊ ጊዜ የሰጣቸው እንደነበረ ተገልጿል።

ሕጉ የሃይማኖት ተቋማቱን በተገቢው ሁኔታ የተደራጁ እንዲሆኑ የሚያዝ ከመሆኑ ባሻገር ስፍራው ደህንነቱ የተጠበቀ እና የድምፅ ብክለትን ማለትም ከፍተኛ መጠን ያለው ድምፅ ማውጫ መጠቅምን የሚያግድ ስለሞኑ ሰምተናል።

በተጨማሪም ሕጉ ማንኛውም ሰባኪ ቤተ እምነት ከማቋቋሙ በፊት የሃይማኖት ትምህርት ስልጠና መውሰዱን ማረጋገጥ ይኖርበታል ማለቱን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው።