71 ሺ የአሜሪካ ዶላር የያዘ ቦርሳ ለባለቤቱ ተመለሰ።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመንገደኛ ተረስቶ የተገኘ ቦርሳ በውስጡ ከነበረው 71 ሺ የአሜሪካ ዶላር ጋር ለሚመለከተው የአየር መንገዱ ቢሮ ያስረከቡት አቶ ለማ በቀለ አለሙ አድናቆት እየጎረፈላቸው ይገኛል።
አየር መንገዱ አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኃላ ንብረቱን ለባለቤቱ ማስረከቡን ድርጅቱ “መሃላ በተግባር” ሲል ካጋራው ጽሑፍ ተመልክተናል።
እንደዚህ ያሉ ዜጎችን ሲገኙ እውቅናና ሽልማት ሊሰጣቸው ይገባል የዝግጅት ክፍላችን መልእክት ነው።