7ኛው ሀገራዊ ምርጫና ሰላም
ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማድረግን ዋነኛ አላማው ያደረገ የኢትዮጵያ ፖሊስ ወንጀል መከላከል አዛዦች ፎረም መቋቋሙን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በፖሊስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቋቁሟል የተባለው ፎረሙ የምርጫ ቁሳቁሶችን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በማድረስ፤ ቁሳቁሶች በደረሰቡት ቦታም ጠንካራ ጥበቃ በማድረግ ኃላፊነቱን በሚገባ መወጣት እንዳለበትም ዛሬ በተካሂደው ምክክር ላይ ተገልጿል።
ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ ከሁሉም የክልልና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ተቋማት የተውጣጡ የፎረሙ አባላት በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር በመተባበር ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ተመልክቷል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
